The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

ቱሉዲምቱ ቁ ት/ቤት፣ኮዬ ፈጬ ቁ.2 እና ቁ3 ት/ቤት እና ገላን ቁ3 (ጮሎ) የአጥር እና ጥበቃ ቤት ግንባታ ስራ፣ የአርቲስት ሃጫሉ መታሰቢያ ት/ቤት የአጥርና መጸዳጃ ቤት ግንባታ ስራ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 20፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የአማካሪ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2013

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት በክፍለ ከተማው በግንባታ ሂደት ላይ ያሉና ሊያስገነባቸው የፈለገውን ግንባታዎች የማማከር ስራ አገር በቀል አማካሪዎችን አወዳድሮ በማዋዋል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቶች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡

  • ሎት 1… ቱሉዲምቱ ቁ ት/ቤት፣ኮዬ ፈጬ ቁ.2 እና ቁ3 ት/ቤት እና ገላን ቁ3 (ጮሎ) የአጥር እና ጥበቃ ቤት ግንባታ ስራ፣ የአርቲስት ሃጫሉ መታሰቢያ ት/ቤት የአጥርና መጸዳጃ ቤት ግንባታ ስራ
  • ሎት 2 ወረዳ 11 መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ወረዳ 12 ቢሮ ግንባታ እና ወረዳ 13 ቢሮ ግንባታ ስራ፣
  • ሎት3 ወረዳ 13 ቱሉዲምቱ ጤና ጣቢያ ቲቢ ከፍል፣ፋርማሲ ክፍል፣ካርድ ክፍል ግንባታ፣ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራ፣ ቂሊንጦ ጤና ጣቢያ ፋርማሲ ክፍል፣ካርድ ከፍል፣ቲቢ ክፍል ግንባታ እና ወረዳ 1 የቢሮ ማስፋፊያ ግንባታ ስራ፣ እና በወረዳ 04 ወረዳ 08 ቤተ መጽሐፍት እና ወረዳ 06 አንድ ማዕከል ግንባታ ቀሪ ስራዎች
  1. ደረጃቸው CAE (ኮንሰልቲንግ አርክቴክት ኢንጂነር) ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ የሆኑ፡፡
  2. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፣ ከኮንስትራከሽን ቢሮ የልዩ ለማማከር ስራ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መጫረት ይችላሉ (ለ2012 የታደሱ) ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉ ሰባት የስራ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን
  • ሀ, ቴከኒካል ሰነደ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ (እያንዳንዳቸው በሰም የታሸጉ)
  • ለ ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ (እያንዳንዳቸው በሰም የታሸጉ) በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲሁም ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ እቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በስምንተኛው የስራ ቀን የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሰረት በዚሁ ዕለት የጨረታ ሰነዱን (Technical and Financial) ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል፣ ኮፒዎቹ ላይ ኮፒ በማለት መጻፍ ያለባቸው እና ሁሉንም ፖስታዎች በሰም ማሸግ ያለባቸው ሲሆን፣ ይህን አለማድረግ ከውድድር ያሰርዛል፡፡

5ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በእቃቂ ቃሊቲ ከ፡ ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond) 5,000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የመንግስት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስይዙትንም (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦሪጂናል ዶክመንት ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

7 በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ስራ ያላቸው የስራ ተቋራጮች በክ/ከተማው ጨረታ ለመሳተፍ የያዙትን ስራ ከ 70% በላይ ማድረሳቸውን መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. የጨረታውን መመሪያ አለማከበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡

9.ከአንድ ሰነድ በላይ መወዳደር፣ ከተወዳደሩበት ሁሉ ላይ ያሰርዛል፤ በተጨማሪም ተጫራቶች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ፣ዋጋ(Rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡

10. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል ::

11. አድራሻ ከቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት በሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ህንጻ ላይ ሁለተኛ ፎቅ የመንግስት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን፡፡

12 ልዩ አማካሪው ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ቢያንስ የሰራተኛውን 40% በክፍለ ከተማው የተመዘገባ ስራ አጥ ባለሙያ ወይም መሃንዲስ መቅጠር አለበት፡፡ ለዚህም መተማመኛ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ደብዳቤ የሚያቀርብ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡

13, አማካሪው ደርጀት የዲዛይን ማሻሻያ፣ የግንባታ ክትትል እና ውል የማስተዳደር ስራ ይሰራል፡፡

14. ኣማካሪ ድርጅቱ ሥራውን በጥራት ለማከናወን የሚከተላቸውን መሰረታዊ ስትራቴጂዎች የሚያቀርብና እነዚህም ባለመፈጸማቸው ተጠያቂ እንደሚያደርገው ማረጋገጫ የጻፈና በስራ አስኪያጅ ወይም በኃላፈው የተፈረመና ማህተም ያለው ሰነድ የሚያቀርብ፡፡

15. ልዩ አማካሪው በደረጃው እንዲያሟላ የሚጠበቅበትን የሰው ሃይል ያለውና በህጋዊ መንገድ በከፍለ ከተማችን የተመዘገቡ ባለሙያዎችን የሚቀጥር መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ እንዲሁም ፕሮጀከቱን በጥራት ለማከናወን በቴክኒክ ሰነዱ ላይ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ባለሙያዎችን በወቅቱ እንደሚያሟላ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ደብዳቤ የሚያቀርብ፡፡

16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የመንግስት

ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና

ግዢ ቡድን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page