| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 20፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ደብረ ማርቆስ ከተማ |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2013
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በUllDP ፕሮግራም በ 2013 በጀት ዓመት ለሚሰሩት የተፋሰስ ግንባታ ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም “RC” Road Contractors OR “GC’’ General contractors ደረጃ 7 እና በላይ የሆናችሁና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተቋራጮች እንድትወዳደሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን ::
| የፕሮጀክቱ ስም | ቀበሌ | ሎት | የፕሮጀክቱ አይነት | መለኪያ | ብዛት | የፓኬጅ ቁጥር |
| ከእንደገም ቄሶች ሰፈር እስከ ጠጠር መንገዱ | 09 | 13 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 452 ሜ | AM/DM/UIIDP/CW/01/20(13) |
| ባታ ከአቶ ገብሬ ባህሪ መኖሪያ ቤት እስከ የግንባን ሸጥ ድረስ | 07 | 4 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 738 | AM/DM/UllDP/CW/01/21(4) |
| ከአቶ ኤፍሬም መኖሪያ ቤት እስከ ውሰታ ወንዝ | 09 | 16 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 452 | AM/DM/ UIIDP /CW/ 01/21(16) |
| ከአብማ ት/ቤት እስከ ውለታ ወንዝ | 03 | 3 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 630 | AM/DM/UlIDP /CW/ 01/21 (3) |
| ከዘሪሁን ቶርኖ ቤት እስከ ወንድሙ እሸቱ መኖሪያ ቤት ከአቶ አበበ ይገረም መኖሪያ ቤት እስከ ሙሉጌታ ይልቃል መኖሪያ ቤት | 06 | 22 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 417 | AM/DM/UllDP /CW/ 01/21(22) |
| ከአቶ ቀለሙ መኖሪያ ቤት እስከ ቀበሌ 07 አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት | 07 | 6 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 396 | AM/DM/UllDP/CW/ 01/21(6) |
| ከቦሌ አሮጌው ተፋሰስ እስከ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን | 08 | 19 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 535 | AM/DM/UIIDP /CW/01/21(19) |
| ከአቶ አደመ መኖሪያ ቤት እና ዶክተር ጥላሁን መኖሪያ ቤት እንዲሁም ቦሌ 20 ሜትር ተፋሰስ እስከ ተክለሃይማኖት 20 ሜትር መንገድ | 08 | 11 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 539 | AM/DM UIlDP /CW/01/21(11) |
| ከአቶ ማሃሪ መኖሪያ ቤት እና በተቃራኒው ስላሲ መሰረተ ክርስቶስ እና ቀጠና 3 ፖሊስ ጽ/ቤትእስከ መሰረተ ክርስቶስ አዲሱ አስፓልት | 7 | 17 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 631 | AM/DM UIIDP /CW/01/21(17) |
| ከቄሴ ሱቅ እስከ የኔ ትምህርት ቤት | 08 | 8 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 524 | AM/DM/UIIDP/CW/ 01/21(8) |
| ባታ አቶ ይሁኔ አለኽኝ መኖሪያ ቤት እስከ ውሰታ ወንዝ | 5 | 11 | ተፋሰስ ግንባታ | ሜትር | 778 | AM/DM/UIIDP /CW/ 01/21(11) |
ስለዚህም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይቻላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN /ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የግዥ መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር በመክፈል ደ/ማ/ከተ/አስ/ከተ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ለእያንዳንዱ ሎት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳብ መቀበያ ቅጹን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ለየብቻው በማሸግ በፖስታው ጀርባ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ብሎ በመፃፍ (በመለየት) ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም ሎቶች በ30 ተከታታይ ቀናት በፖስታ በማሸግ ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለያንዳንዱ ሎት ብር 30,00.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች እራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ለሁሉም ሎቶች ጋዜጣው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ30ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ 9፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 30ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ለመክፈት አይስተጓጎልም::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581780067 ወይም 0581780040 ወይም በፋክስ ቁጥር 0587713057 በመላክ ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 049 በጽሁፍ መጠየቅ ይቻላል ::
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት