| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 14፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እጅግ ዘመናዊ የሆነ በ3500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ለአረጋውያኑ ለአእምሮ ህሙማኑ መኖሪያ እና ህክምና መስጫ የሚሆን ሆስፒታል 2B+G+10 የሆነ ፎቅ እና በአዲስ አበባ 10ሩም ክፍለ ከተሞችና በክልል ከተሞች በማስፋፋትና ተጨማሪ ወገኖችን ከጎዳና በማንሳትና በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ለዚህ ግንባታ የሚውል
- ገልባጭ ሲኖትራክ መኪና፣ ገልባጭ አይሱዙ
- ፌሮ ብረት፣ ሪድ ሚክስ ኮንክሪት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፡-
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር tin Mumber/ ያላቸው፣ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ የሚያቀርቡትን ዋጋ የጨረታ ሰነዱን ከማዕከላችን ቢሮ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ወስደው ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ8ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ተዘግቶ በእለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ነገር ግን 8ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሄራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር :- 8131 /0940494949/0940737373 ይደውሉ፡፡
መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ
ህሙማን መርጃ ማዕከል