| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 8፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ.
Commercial Nomminees PLC
CN/NCB/06/2013
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለጸውን የህንጻ ውስጣዊ ዲዛይን ስራ የተለያዩ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
*** ገርጂ የሚገኘውን ህንጻ ውስጣዊ ዲዛይን ስራ (interior designs and supervision of Building maintenance and Fence work).
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት እና ቲን ሰርተፍኬት፡፡
- በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፡፡
- ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠ የግንባታ ዲዛይንና አናላይዝ ፍቃድ፡፡
- ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያለው::
- ሶስት አመት በተመሳሳይ ዲዛይንና አናላይዝ ስራ ልምድ ያለው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 20,000.00፡፡
- በመሆኑም ከላይ የተገለጹትን ዝርዝር ቴክኒካል ዶክመንቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቴክኒካል ዶክመንቶችን በሰም በታሸገ የተለየ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንዲሁም የመጫረቻ ዋጋ (ፋይናንሻል ዶክመንት) በሰም በታሸገ ሁለተኛ ሌላ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- የጨረታ ዶክመንቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተክለኃይማኖት ቅርንጫፍ በሚገኝበት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 118 ሎጅስቲክስ እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00 -6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00 – 11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተክለሀይማኖት ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንጻ ::
ስልክ ቁጥር 011-1-56 52 08
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር