| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 5፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
Remaining Time for Bid Submission: Not Fixed
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን
ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ
አገልግሎት ግዥ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር :- ማ/ኪ/አ/ግ 01/2013
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግንባታ ማሽነሪዎችንና ተሽከርካሪዎችን በቁርጥ ዋጋ ተከራይቶ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች በሚገኙ የመንገድ፣ የግድብና መስኖ፣ የህንጻ ፣ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ የደረቅ ወደብ እና ሌሎች የመሰረት ልማት አውታር ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ በኪራይ አሰማርቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
| ገልባጭ | ዶዘር |
| ገልባጭ (ኳሪ/የድንጋይ መኪና) | ግሪደር |
| የውሃ ቦቴ | ሮለር |
| ቼን ኤክስካቫተር | ሎደር |
| ኤክስካቫተር ባለጃክሃመር | የድንጋይ መሰርሰሪያ(ዋግንድሪል) |
| ባለጎማ ኤክስካቫተር | ሳንድ ሜከር ክሪሸር |
በዚሁ መሠረት እንደ የፕሮጀክቱ ተጨባጭ ሁኔታ ተጠንቶ በተዘጋጀው የቁርጥ የኪራይ ዋጋ መሣሪያዎችን ለማከራየት የምትፈልጉ የመሣሪያ አከራዮች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በማንኛውም የሥራ ሰዓት(ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) ቃሊቲ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና ማሽነሪ አስተዳደር ዘርፍ በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አከራዮች በምዝገባው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- አከራዮች በምዝገባው ለመሳተፍ የባለቤትነት ደብተር/ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉና በውክልና ከሆነ ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አከራዮች ማቅረብ በሚችሉት የመሣሪያ ብዛት ያለገደብ በፈለጉት ፕሮጀክትና ዲስትሪክቶች መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- በምዝገባው መሣተፍ የሚችሉ አከራዮች መሣሪያዎቻቸውን እንዲያሰማሩ ትዕዛዝ በደረሳቸው በ 1(አንድ) ሣምንት ጊዜ ውስጥ በሥራ ቦታው ማድረስ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ያልተመዘገቡ አከራዮች ለሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፊኬት ማግኘት ሲችሉ ሰርተፊኬቱንም ሲመዘገቡ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በምዝገባው ለመካፈል የሚፈልጉ አከራዮች ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች በተጨማሪ የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ከሚፈልገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የማሽነሪዎችንና ተሸከርካሪ ዝርዝር መረጃ፣ የኪራይ ዋጋቸውን እንዲሁም የፕሮጀክቶቹን ዝርዝር በምዝገባው ወቅት በአካል ማየት ይቻላል
- ምዝገባው የሚካሄደው ቃሊቲ በሚገኘው የኪራይ መሳሪያ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሲሆን መ/ቤቱ የሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከተሽከርካሪዎች ማሰልጠኛው ወረድ ብሎ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት ጎን ነው::
- በአንድ መሣሪያ መመዝገብ የሚቻለው ለአንድ ፕሮጀክት ነው፡፡
- ለገልባጭ መኪኖች የመጫን አቅም ከ 12 ሜ/ኩብ እና በላይ መሆን አለበት፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች/ማስረጃዎች አሟልቶ ለመመዝገብ የቀረቡ አከራይ ድርጅቶች የመሣሪያ/የተሽከርካሪ ፍላጎት ባልተሟላላቸው ፕሮጀክቶች ምደባ በቀጥታ የሚሰጠው ሲሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ቅድሚያ ለተመዘገቡ አከራይ ድርጅቶች ይሆናል፡፡ ምዝገባው የማሽነሪ ፍላጎቱ እስኪሟላ ድረስ ክፍት ሆኖ ያለጊዜ ገደብ ይቆያል፡፡
- አከራዮች ለመመዝገባቸው ሰነዱ ላይ በስማቸው አንጻር መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ የአገልግሎት ግዥውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ተመዝጋቢዎች የሚከተለውን አድራሻመጠቀም ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የኪራይ መሳሪያ አስተዳደር ቡድን ቢሮ
የስልክ ቁጥር ፡-0118694016/0989815730
የኋላውን እያደስን የወደፊቱን እንገነባለን!!
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን