The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

ለ ባለ 12 ፎቅ መንትያ ሕንፃዎች እና አንድ ባለ 4 ፎቅ አፓርታማ እና በስሩ ላሉ ክፍሎች ለእያንዳንዱ ነዋሪ የራሱ የውሃ ቆጣሪ እንዲኖረው ለማድረግ ከሕንፃዎቹ ውስጥ ለሚገኙ አንድ መቶ ሰማንያ ክፍሎች የውሃ መስመር ዝርጋታ

Published on: Reporter ( መስከረም 20፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:Addis Ababa

Remaining Time for Bid Submission

በሕንፃዎች ውስጥ ለሚገኙ ክፍሎች የውሃ መስመር ዝርጋታ ለማሰራት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት በሚያስተዳድራቸው አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ባለ 12 ፎቅ መንትያ ሕንፃዎች እና አንድ ባለ 4 ፎቅ አፓርታማ እና በስሩ ላሉ ክፍሎች ለእያንዳንዱ ነዋሪ የራሱ የውሃ ቆጣሪ እንዲኖረው ለማድረግ ከሕንፃዎቹ ውስጥ ለሚገኙ አንድ መቶ ሰማንያ ክፍሎች የውሃ መስመር ዝርጋታ በጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል፡፡ 

አድራሻ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ከዳግማዊ ሚንሊክ ት/ቤት ፊት ለፊት ሮሚና እና ማለዳ ካፌ አጠገብ፡፡ 

  1.  ድርጅቱ ሊያሰራ የፈለገውን የውሃ መስመር ዝርጋታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመሥራት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሕንፃዎቹ ሥር የሚገኙ ክፍሎችን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት። 
  2.  ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ ፈቃዱን ከንግድ ፈቃዱ ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡ 
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ሥራ ከሚሰጡት ጠቅላላ ዋጋ 15% (አስራ አምስት በመቶ) የሚሆነውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
  4. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል :: 
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው :: 
  • ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0111 56 63 37 ወይም 
  • በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ፡፡ 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page