Published on: Addis Lessan ( መስከረም 21፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጋሞ ዞን
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የ2013 ዓ.ም ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውል
- የጽ/መሣሪያ፣ የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- የሕንፃ መሳሪያዎች ፣ የግንባታ ዕቃዎች ፣
- የቤትና የቢሮ ዕቃዎችና የግንባታ ሥራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚያስፈልጋቸው፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣
- የነጋዴ መለያ ቁጥር ያለው/ያላት፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፣
- የዋጋ ማቅረቢያ በእያንዳንዱ ዕቃ ነጠላ ዋጋ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾች የመልካም ሥራ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ጨንቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ድረስ ማድረስ ይኖርበታል፡፡
- ቫት በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ካልተገለፀ እንደተገለፀ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- የቀረበው ዕቃ ጥራቱን የጠበቀ ካልሆነ አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ውል ከመግባቱ በፊት ናሙና ዕቃዎችን ማቅረብ አለበት፡፡
- የማስጫኛና የማውረጃ ወጪዎችን በአሸናፊው ድርጅት ይሸፈናል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ጨንቻ ወረዳ ዙ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችል/የምትችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት በ22ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ስለሆነም 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ /Bid bond/ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ በየሎቱ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው ዋጋ ከውል ጊዜ ጀምሮ ለዘጠና ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
- የአሸናፊ ድርጅት ውል ለመግባት ሲመጣ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡ ማሳሰቢያ፡በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467760362/0916345359 መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት