Published onBe’kur ( መስከረም 18፣ 2013 ): /Place of Bid Competitions:ጐንደር
Remaining Time for Bid Submission
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጐንደር ዞን በእብናት/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለእብናት ወ/ት/ት/ጽ/ቤት
- ለእብናት 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ለመማሪያ ክላስ አገልግሎት የሚውል G+3 ግንባታ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የም ታሟሉ ሁሉ መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ ድምር 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ/ሲፒኦ/ በእብናት ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ል/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ወይም/በጥሬ ገንዘብ እብናት ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጐ መቅረብ አለበት፡፡ ደረቅ ቼክ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ/ፖስታ/ ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት እብናት ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ ለ21 ቀን በአየር ላይ ውሎ በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ታሽጐ 5፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ/የህዝብ በዓል ከሆነ/ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ለስራ በተፈለገበት ሰዓት ለ3 ቀናት ተጠብቆ ካልቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ መሆን ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ አንዱን ያልሞላ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 08 የማይመለስ 500 ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 40 ቀን ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 4400606/218 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእብናት/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
በኩር