Published on: Addis Zemen ( መስከረም 3፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission
የሞተር ግሬደር ኪራይ ጨረታ
ኮርፖሬሽናችን ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር ለሚያከናውነው የመሬት ምንጣሮ ድልዳሎ (Precise Land leveling) ሥራ አገልግሎት የሚውል 160 እና ከዚያ በላይ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን ግሬደሮች በዘርፉ አግባብነት ያለውና በ2011 ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ ከሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች :
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኮርፖሬሽኑ የግብርና ሜካናይዜሽንና ኢንጅነሪንግ ዘርፍ ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት መግዛት ይችላል ::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖረው 15ተኛ ቀን ላይ ከቀኑ 7፡45 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚኖረው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት የሚያቀርቧቸውን የመሳሪያ ዓይነቶች ዝርዝር በሠዓት የኪራይ ተመን ዋጋ በመሙላት እንዲሁም አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎችና ሰነዶችን ኮፒ በአንድ ላይ በማያያዝዝና በሰም በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
- ጨረታው በተራ 2 ላይ በተቀመጠው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ሜካናይዜሽንና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ቢሮ በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ የመከፈቻ ስነ ስርዓቱ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከናወን ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ጋር የሚያቀርበውን የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO ማስያዝ ይኖርበታል .
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቀጥር 011 442 23 60 ወይም 011 442 54 83 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ.
የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ሜካናይዜሽንና
ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ከኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ በስተጀርባ
በኢትየጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የግብርና ሜካናይዜሽንና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ