Published on: Addis Zemen ( መስከረም 3፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:ባህርዳር
Remaining Time for Bid Submission
የአልሙኒየም ፓርቲሽን ስራ
ግዥ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሠነድ ቁጥር፡- አዲቁሥድ – 06/2013
አማራ የዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት የአንድ የስራ ክፍል የቢሮ ውስጥ ለውስጥ ክፍሎችን በአልሙኒየም የፓርቲሽን ስራ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማስራት ይፈልጋል::
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሚጠይቅ ከሆነ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህርዳር ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 025 በመቅረብ ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ መስከረም 19/2013 ዓ.ም ድረስ መግዛት ይችላሉ::
- ጨረታው መስከረም 19/2013 ዓ.ም. በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8:30 ሰዓት ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በጥሬ ገንዘብ፣በሲ.ፒኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ እና ህጋዊ ማስረጃዎችን በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 023 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ::
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058-218- 02- 73 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 ወይም 058-218-05-60 በመላክ መጠየቅ ይቻላል ::
አማራ የዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት፣
ባህርዳር-ኢትዮጵያ