Remaining Time for Bid SubmissionNew!
Remaining Time for Bid Submission
| Invited Grade: | GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ |
| Place of competition: | ሀዋሳ |
N.B Please check the above countdown time ,Competition place & invited Grade before usage.
| Published on: | Addis Zemen ( ግንቦት 14፣ 2013 ) |
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 08/2013
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት በመልጋ ወረዳ ጉጉማ ቀበሌ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት
- ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ የሥራ ተቋራጮች 2013 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TN NO/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው መንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ | VAT/ ተመዝጋቢ እና የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሰሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈጻፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴከኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid security) ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሥሪ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴከኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቬሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁለም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፤ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታው መከፈት አያግደውም።
- አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
መረጃ፡-046 212 4307 ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ
Good Luck!