| Published on:Reporter ( ታኅሣሥ 4፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አድዋ ፓርክ ሳይት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኃ.የተ.የህ. ሥራ ማህበር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘዉን 10 የጋራ የመኖሪያ ቤት እድሳት ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ማህበሩ ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ስለሚፈልግ መስፈርቱን የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ተቋራጮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታዉን ሰነድ በማህበሩ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰአት በመግዛት እንድትሳተፉ ይጋብዛል ::
ስለሆነም:
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ግቢዉ ዉስጥ በሚገኘዉ ቢሮ በመገኘት መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ምከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል ::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ::
- ስለ ሥራዉ አጠቃላይ ዝርዝር ከጨረታዉ ሰነድ ዉስጥ ይገኛል፡፡
አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደዉ መንገድ የድሮው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ሳሚ ህንጻ ጀርባ ባለው መግቢያ ገባ ብሎ።
ማሳሰቢያ: ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል፣ አንድ ቴክኒካል ኮፒ፣ ፋይናኒሻል ኦርጂናል አንድ ፋይናኒሻል ኮፒ እና ሲፒኦ ለብቻ በሰም በታሸግ ኢንቨሎፕ ታሽጎ ቴክኒናል በአንድ “ኤንቨሎፕ ፋይናኒሻል በአንድ ኢንቨሎፕ ሁሉንም በአንድ በሰም በታሸገ እናት ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116394463
የማህበሩ አስተዳደር ጽ/ቤት