The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

ጠጠር የሚያመርት ክሬሸር ኪራይ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 12፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ባህ/ዳር
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

ክሬሸር ተክሎ ጠጠር የሚያመርት የኪራይ ግዥ እና

ቢትመን ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር አመሥድ 18/2013

ድርጅታችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፀውን ክሬሸር ተክሎ ጠጠር የሚያመርት የክሬሸር ኪራይ እና የተለያየ ቢትመን ግዥ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ.የአገልግሎቱ አይነትብዛትየሚሰራበት ቦታ(ፕሮጀከት)ምርመራ
1ጠጠር የሚያመርት ክሬሸር ኪራይ01 ለጎንጅ ቆለላ (ኮሬ አዲስ አለም ፕሮጀክት) 
2የተለያየ ቢትመንበጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለጽለደንበጫ ፈረስ-ቤተ እና ደሴ ከተማ 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የተእታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር እና ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ90 ቀን የሚቆይ ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ የተእ.ታክስን ጨምሮ ለክሬሸር ኪራይ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ለቢትመን 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የጠጠር እና የቢትመን መጠን እንደነስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ አተገለጸው ክሬሸር አስፈላጊ መረጃዎችን መጥቀስ እና ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም ለቢትመኘ የዋጋ መሙያ (ፋይናንሻል) ሰነዳቸውን ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ እንዲሁም የክሬሸር የዋጋ መሙያ (ፋይናንሻል) እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና ሌሎች የክሬሽሩን የቴክኒካል ሰነዶችን (ሊብሬ)እና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በተጨማሪም የጨረታ ማስከበሪያቸውን ለብቻ በፖስታ አድርገው በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕርዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ይሁን እንጂ 20ኛው የመክፈቻ ቀን ከድርጅታችን የስራ ሰዓት ውጭ ከሆነ እና የመንግስት ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. በጨረታው ለተገለፁት እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. የድርጅታችን የቴክኒካል ሰነድ ከፋይናንሻል መሙያ ሰነድ ጋር አያይዘናል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-220-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት

ባህ/ዳር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page