Published on: Addis Zemen ( መስከረም 21፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:ባህር ዳር
Remaining Time for Bid Submission
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ በባህርዳር ውስጥ እያስገነባ ለሚገኘው የብረታ ብረት ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ ጠጠር እና አስፓልት GC-6 ወይም RC-6 እና ከዛ በላይ የሆኑትን ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት ለጨረታ ለመወዳደር ይቻላል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በፖስታ በማሸግ እና ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 (ሀያ) ቀናት የቀድሞው ግብርና ሜካናይዜሽን ወርክ ሾፕ ባህርዳር ዙሪያ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ባህርዳር ማምረቻ ተቋም ግቢ በሚገኘው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 10 የመቅረብ ሰነዱን በ200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በመውሰድ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 50000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለ20 (ሀያ) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ21ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰአት ይዘጋና በዚያው ቀን ከተዘጉበት ከ30 ደቂቃ በኋላ ይከፈታል፡፡ 21ኛው (ሀያ አንድ) ቀን በአል ወይም እሁድ ከሆነ በማግስቱ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመወዳደሪያ ሰነዱ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ ለኢንተርፕራይዛችን ቢደርስ የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ ባህር ዳር በስልክ ቁጥር 058 226 6315/ 058 220 0631 መጠቀም ይቻላል፡፡
የአብክመ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ
ባህር ዳር