Published on:Addis Zemen ( ጳጉሜ 3፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:ደባርቅ ከተማ
Remaining Time for Bid Submission
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት፤ ቤቶችና ኮንስ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በክልሉ፤ በከተማው እና በዓለም ባንክ በጀት ድጋፍ በከተማው የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በ CIPO ዕቅድ መሠረት በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
*የድሬኔጅ ግንባታ PACKAGE NUMBER- AM/DEBARK UIIDP /CW-03/20/21
- ከኃይሌ ጎሽ እስከ ዘነብ ዘገየ ቤት ከ2 ክሮስ ስላብ ጋር በሜትር 231 ሎት 1
- ከጣመ ዘውዱ እስከ ሚሊኒም መንገድ ከ2 ክሮስ ስሳብ ጋር በሜትር 264 ሎት 3
የግራብል ሮድ ግንባታ PACKAGE NUMBER- AM/DEBARK CIP/ CW-10/20/21
1. ከአስፖልቱ እስከ ዋሊያ ስላብ ክልበርት በሜትር 809 ሎት 2 የሜንቴናስ ግንባታ PACKAGE NUMBER- AM/DEBARK CIP/ main-01/20/21
- የሚዲያን ስትሬት ላይት ሜንቴናስ በቁጥር 40 ሎት 4
- የስታዲም ስቴር ሜንቴናስ M21500 ሎት 8
- የሪቴኒግ ወል ሜንቴናስ ሚሊኒም ት/ቤት አካባቢ M2 290.69 ሎት 9
- የሪቴኒግ ወል ሜንቲናስ MSE SHADE አካባቢ M 2 465. ሎት 10
ከላይ የተዘረዘሩ ግንባታዎች ባለሙያ ባወጣው ስፔስፊኬሽን መሰረት በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማስገንባት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የታደስ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የቫት ተመዝጋቢ፣ የሙያ ፍቃድ ያለውና የታደሰ፡፡
- ተጫራቾች ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እና ለስትሬት ላይት ሜንቴናስ የኤሌክትሮ መካኒካል ጠ/ስ/ተቋራጭ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በበጀት ዓመቱ አዲስ ፍቃድ ካላወጡ በስተቀር ማንኛውም ተጫራች የመልካም ሥራ አፈፃፀም መረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ ለእያንዳንዱ ለድሬኔጅ ሎት 1 ብር 10,830 ፤ ሎት 3 ብር 12,218፣ ለግራብል ሮድ ግንባታ ሎት 2. 12,013 ብር ፣ የሜንቴናስ ግንባታ ሎት 4 ብር 13,500፣ ሎት 8. 7,312 ብር ሎት 9 3,750 ብር፣ ሎት 10. 6,000 ብር ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በመሂ፡ የተቆረጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሆኖ መረጃውን ከኦርጂናል ፖስታው ውስጥ አስገብተው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::
- የመጫረቻ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 የሥራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቻልም፡፡
- በማህበር ተደራጅተው ለሚወዳደሩ በጨረታው እንዲወዳደሩ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ በአደራጃቸው ተቋም ማምጣት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 ከ3/13/2012 ዓ.ም እስከ 18/01/2013 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በብር 100 (አንድ መቶ ብር) መግዛት ይቻላል፡፡ እንዲሁም ከቴክ/ሙያ/ኢንተር/ል/ጽ/ ቤት ተደራጅተው ለሚመጡ በነፃ የሚሰጥ መሆኑን ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 እስከ 19/01/2013 ዓ.ም እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ወይም ከዚያ በፊት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ቢሮ ቁጥር 13 በተገለጸው ቦታ በ19/1/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ወይም ጨረታ ሰነዱን ፊርማና ማህተም በማድረግ በፖስታ ታሽጎ አንድ ወጥ የሆነ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካለ በጽ/ቤቱ የውስጥ ሰሌዳ የምናሳውቅ መሆኑ፡፡
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 058 117 0033/0581171208 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት፤
ቤቶችና ኮንስትራክሽን /ጽ/ቤት