| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 6፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ቤኒሻንጉል ጉሙዝ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 07/2013
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ለ2013 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሶስት ዞኖች ለመተከል ዞን ፣ አሶሳ ዞን እና ካማሽ ዞን ውስጥ ለውስጥ በመንገድ ከፈታ እና በመንገድ ጥገና ሥራ ላይ ማሽንሪዎችን ተከራይቶ ለማሰራት ይፈልጋል
በዚሁ መሠረት፦
| ተ.ቁ | የመሳሪያዎች አይነት | ብዛት | የሥራው መለኪያ | ዓመታዊ የሥራ መጠን /በሰዓትና በቀን/ |
| 1 | ዶዘር | 2 | ሰዓት | 2496 |
| 2 | ግሬደር | 3 | ሰዓት | 3744 |
| 3 | ሩሎ | 3 | ሰዓት | 3744 |
| 4 | ሎደር | 3 | ሰዓት | 3744 |
| 5 | የውሃ ቦቴ | 2 | ቀን | 312 |
| 6 | የሰርቪስ መኪና ፒካፕ | 4 | ቀን | 624 |
| 7 | ገልባጭ መኪና | 9 | ቀን | 1404 |
ከላይ የተገለጹትን የመሳሪያዎችን በሰዓትና በቀን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል ::
በዚህም መሰረት፡
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በበጀት ዓመት ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የምትችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላችሁ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገባችሁ መሆናችሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::
- የሚያከራዩን መሳሪያዎች የራሳቸው ለመሆኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም አግባብ ባለው ሙሉ የህግ ውክልና ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራች ተከራይ የጠየቀውን የማሽን ቁጥር/ብዛት/ በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ግዴታ አለበት።
- በመስኩ ስራ ላይ ለመሰማራታችሁ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚትችሉ ሁሉ ይህንን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው በኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ዲዛይን ቁጥጥር ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት (አስራ አምስት) ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው ቀን) ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይ ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግና በማሽግ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው በኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ዲዛይን ቁጥጥር ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል ሰነዱን ይዞ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የሚያከራዩትን ማሽኖች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ) ኮፒው እና የውክልና ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ እና በእርሳስ የተሞላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም:: የሚቀርበው ዋጋ ከ5% ቫት በፊት ወይም ከቫት በኋላ ተብሎ በግልጽ ተጽፎ መቀመጥ አለበት ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በተመለከተ ለዶዘር 100,000 ብር /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለግሬደር 75,000 ብር/ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ለሩሎ 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሎደር 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር /ለውሃ ቦቴ 12,000 ብር /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሰርቪስ መኪና ፒካፕ 30,000 ብር /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለገልባጭ መኪና 100,000 ብር/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው:: በመሆኑም ከባንክ ከተረጋገጠ CPO ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የስልክ ቁጥር 0577752622
አሶሳ
የቤ/ጉ/ክ/መ/መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን