| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 1፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አአማ01/2013
የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚያስገነባው የጣርማ በር መንገድ ስራ ፕሮጀክት የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችንና ተሽከርካሪዎችን ማለትም
- ዶዘር፣ ኤክስካቫተር ከነጃክ ሀመሩ፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ገልባጭ መኪና፣ የውሃ ቦቴ፣ ሰርቪስ መኪና(መለስተኛ አውቶቡስ) እና የመስክ መኪና (ደብል ካፕ/ሚኒ ካፕ/ሲንግል ካፕ) ህጋዊና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችና ማሳሰቢያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በሚወዳደሩበት የኮንስትራክሽን መሳሪያ የተመዘገበ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር(ሊብሬ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ተደርገው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚቀርቡት ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸው፣ የመጫን አቅማቸው፣ የነዳጅ ፍጆታቸውና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለበት፡፡
- የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
- ለኪራይ የሚቀርቡት ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች በናፍታ የሚሰሩ ብቻ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታና የውል ማስከበሪያ የሚውል ሲፒኦ (CPO) ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ማሽንና ተሽከርካሪ በተጠቀሰው የብር መጠን ልክ በብሔራዊ ባንክ እውቅና ከተሠጣቸው ባንኮች ብቻ አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) በድርጅታችን ስም አማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (AMHARA BUILDING WORKS CONSTRUCTION ENTERPRISE) ተብሎ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ/አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጀርባ ካለው አልማ ህንጻ ከሚገኘው በአሕሥኮድ የአ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር፡- 011-1265652/011-126 5145/ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዱን) “ዋና እና ቅጅ” ለየብቻ በመለየት አንድ ወጥ በሆነ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ በግልፅ የሚታይ የተጫራች ድርጅቱን ማህተም በመወዳደሪያ ሰነዱ እያንዳንዱ ገጽ ላይና በማሸጊያ ፖስታው ላይ በመምታት አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጀርባ ካለው አልማ ህንጻ ከሚገኘው በአሕሥኮድ የአ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግራውንድ ፍሎር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት በአሕሥኮድ የአ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግራውንድ ፍሎር ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ተከታታይ ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ሊኖር ይገባል፡፡
- ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- በጨረታ ውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት የሚያከራየውን ተሽከርካሪም ሆነ ማሽነሪ በራሱ ወጭ (ትራንስፖርት) መንገድ ግንባታ ቦታው ድረስ በማጓጓዝ ያቀርባል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
በስልክ ቁጥር 011-126 5652/011-126 -5145 በመደወል ወይም
በፋክስ ቁጥር 011-126 5338 በመላክ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
አዲስ አበባCompany Info