Published on:Addis Zemen ( መስከረም 16፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:አዋሳ
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደመባ 02/13
መ/ቤታችን የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ሲቪል ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም
- ዶዘር፡ ግሬደር ፣ ኤክስካቫተር ፣ ሮለር እና ሎደር ብቁ ተጫራቶችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት፣ የመንግሥት መ/ቤቶች በሚያወጡት የጨረታ ማስታወቂያ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቶች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ «ኦርጅናል» እና «ኮፒ» በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቶች የየሎቱን ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 8 መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ፖስት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል አጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። እለታ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ለኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን
አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት
የፖስታ ሳጥን ቁጥር 688
የሰልክ ቁጥር 046 220 5591/046 22098 90
የፋክስ ቁጥር 046 22 23 66/046 320 2913
አዋሳ ኢትዮጵያ
የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን