| Published on:Reporter ( ጥቅምት 29፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check It!
የጨረታ ቁጥር 007/2012
የጨረታ ማስታወቂያ፧
ድርጅታችን ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ደብረብርሃን ለሚገኘው ፋብሪካው የፍሳሽ ማጣሪያ ፕላንት ግንባታ ሥራ በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ተቋራጮች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውና ከዚህ በፊት ሥለሰሯቸው ሥራዎች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ተቋራጮች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሠነድ አዲስ አበባ – 22 ዲዩቲ ፍሪ ጎን በሚገኘው የፋብሪካው ዋና መ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) ከፍሎ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጸዕን ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኣዲስ ኣበባ 22 ዲዩቲ ፍሪ ጎን በሚገኘው የፋብሪካው ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4:30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል:: የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀናት ላይ ካረፈ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116591249 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
ድርጅቱ