| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 6፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ፌ/ፖ/ኮ19/2013
የኢፌዲሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለ2010 በጀት ዓመት ለወንጀል ምርመራ አገልግሎት የሚውል: የDNA ላብራቶሪ ፓርቲሽን እንዲሰራ እና ፈርኒሽ ለማስደረግ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ ወቅታዊ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት እንዲሁም ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ፌ/ፖ/ኮ 19/2013 የDNA ላብራቶሪ ፓርቲሽን እንዲሰራ እና ፈርኒሽ ለማስደረግ 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት (BID BOND) /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፌ/ፖ/ኮ 19/2013 የDNA ላብራቶሪ ፓርቲሽን እንዲሰራ እና ፈርኒሽ ለማስደረግ እስከ 21/04/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዲቪዥን ቢሮ ቁጥር 203 ቀርበው የጨረታ ሠነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ወይም በመልዕክት ሣጥን ቁጥር 199 መላክ ይችላሉ፡፡ መ/ ቤታችን ስለጨረታ ሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከላይ በተገለፀው የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው በተመሳሳይ ቀን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት ትንሹ አዳራሽ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር
- 011-5-58-17-39/011-5-52-44-12/011-5-31-20-95/011-5-31-21-99 የውስጥ ስልክ 2104/1107/1101 ፋክስ ቁጥር 011-5-52-55-17 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል
ፖሊስ ኮሚሽን