| Published on:Reporter ( ኅዳር 6፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የህንጻ እድሳት ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር FEACC 002/2013
የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለቢሮ አገልግሎት የሚጠቀምበትን ካዛንችስ የቀድሞ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሱፐር ማርኬት ህንጻን የውስጥና የውጭ ሙሉ እድሳት ለማድረግ፣ ጣራወን(Felincote)፣ የግቢውን ወለል (Teraro Ties)፣ እና አጥሩን (በኤጋ ቆርቆሮ ወይም በተመሳሳዩ) ለማሰራት በደረጃ-6 የግንባታ ዘርፍ ላይ ልምድ ያላቸውን እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ስራ ተጫራቾችን በጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ከግንዛቤ በመውሰድና ስራዎቹን በኣካል በቦታው ተገኝታችሁ በመመልከት የስራውን ዝርዝር ዋጋና ስራውን ሰርቶ በማጠናቀቅ ለማስረከብ የሚፈጅባቸሁን ጊዜ ገልጻችሁ የቴክኒክና የዋጋ መወዳደሪያ ሃሳባችሁን በሁለት የተለያዩ ኤንቨሎፖች እንድታቀርቡ በጨረታው የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነዳችሁ ጋር አያይዛችሁ የምታቀርቧቸው ሰነዶች፡
1. በኮሚሽኑ ዋናው ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ፋይናንስ ቡድን ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈልና የጨረታ ሰነዱን በመወለድ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገኘውን የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል መግቢያ ቅጽ እና ምዕራፍ 1 ክፍል 4 የጨረታ ማቅረቢያ ቅጾችን ሞልቶ ማቅረብ፣
2. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ፣
3. የተጨማሪ ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ኮፒ፣
4. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬትና መለያ ቁጥር (Tin No) ሰነድ ኮፒ፣
5. በመንግስት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ ለመንግስት እቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማረጋገጫ ሰነድ፣
6. ከመንግስት የግብር ዕዳ ነጻ መሆናቸው (Tax Clearance) ማረጋገጫ ኮፒ፣
7. የጨረታ መስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ (CPO) የጨረታ ሰነድ አቀራረብ
8. ከላይ ከ1 እስከ 7 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ ከትቶ በማሸግ በኤንቨሎፕ ፊት ለፊት የቴክኒክ መወዳደሪያ የሚል ጉልሕ ጽሁፍ በማኖር ማቅረብ፣
9. የፋይናንስ መወዳደሪያ ሃሳብ የያዙ ሰነዶቻቸውን በሌላ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአንቨሎፕ ፊት ለፊት የፋይናንስ መወዳደሪያ የሚል ጉልሕ ጽሑፍ በማኖር ማቅረብ፣
የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜና የጨረታ አከፋፈት ስነ ሰረዓት
10. የዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ባለው ጊዜ ድረስ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እንዲያቀርቡ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
11. ተጫራቾች በኮሚሽኑ ቢሮ 4ኛ ፎቅ የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 403 በመቅረብ የዋጋ እና የቴክኒክ የመወዳደሪያ ሃሳብ የያዙ ኤንቨሎፖችን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
12. ይህ ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋል በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ አዳራሽ ጨረታው ተከፍቶ የተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሃሳብ የያዙ ኢንቨሎፖች ብቻ ተከፍተው ሰነዶቹ በንባብ ይሰማሉ፡፡
13. የተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ ተገምግሞ መስፈርቱን ያለፉና ያላለፉ ተጫራቾች ውጤትን እና የዋጋ መወዳደሪያ ሃሳብ የያዙ ኤንቨሎፖች መክፈቻ ጊዜን በደብዳቤ ለተጫራቾች ከተገለጸ በኋላ የጨረታ ዋጋ መክፈቻ ስነስርዓት ዕለት በቴክኒክ ያለፉ ተጫራቾች ብቻ የፋይናንስ ኤንቨሎፕ ይከፈታል፤
14. ኮሚሽኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፤
አድራሻ፡- ለገሐር ከበድሉ ህንጻ ጀርባ ወይም ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋናው ቢሮ በጀርባ በር ፊት ለፊት
ስልክ(251 5-53 69 07) (251 5-52 77 83)
የፌደራል የስነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን