The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የጠጠር መንገድ ሰራ

Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 6፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለገላን ከተማ አስተዳደር የጠጠር መንገድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በ2013 የበጀት ዓመት ለማሰራት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1.  ደረጃው አርሲ-5ጂሲ-5( RC-5/GC-5/ እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጭ የሆነ
  2. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድና ሥራ ፍቃድ ያለው
  3. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
  4. የቫት/የተጨማሪ እሴት ታክስ/ተመዝጋቢ የሆነ
  5. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin/ ተመዝጋቢ የሆነ
  6. ስለመልካም ሥራ አፈጻጸም በግንባታ ዘርፍ የሰሩበት መረጃ ቢያንስ ሶስት መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተሰጠ መረጃ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ) በመክፈል በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከገላን ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ቀርቦ መግዛት ይችላል። ነገር ግን የጨረታ ሰነዱን ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላል።
  7. የ2013 ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ለውድድር ያስገባችሁትን ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴከኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ በቁጥር እና በፊደል ያለምንም ስርዝ እና ድልዝ በመሙላት ስም ፣ ፊርማ እና ማህተም ሰነድ ላይ ማኖር አለባቸው።
  11. ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነት ከተገለጸላቸው በኋላ በተገለጸላቸው ቀን ቀርበው ውላቸውን ካልፈጸሙ የጨረታው ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  12. . ይህ ጨረታ በማስታወቂያ በወጣ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል። በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ስነ ስርዓትን አያስተጓጉልም።
  13. የመንግስትን የፋይናንስ መመሪያን የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም ::
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. .ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር- 0114450182 ደውለው ይጠይቁ ::

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

መስተዳድር የገላን ከተማ አስተዳደር

ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page