| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 4፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር 02
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በሴፍቲኔት ካፒታል በጀት ከዚህ እንደሚከተለው ባቀረቡት መሰረት
- ተ.ቁ 1. ሎት ሲሚንቶ፣
- ተቁ 2 ሎት 2 የግንባታ እቃዎች፣
- ተ.ቁ፡ 3. ሎት 3 የውሀ እቃ፣
- ተ.ቁ፡ 4. ሎት 4 ድንጋይ አሸዋ እና ጠጠር፣
- ተ.ቁ፡ 5 ሎት 5 ብሎኬት፣
- ተቁ 6. ሎት 6 የተለያዩ እንጨቶችን፣
- ተ.ቁ 7 ሎት 7 የገጠር ንጹህ መጠጥ ውህ ግንባታ 1
- ተ.ቁ 8. ሎት 8 የመስኖ ግንባታ ፣
- ተ.ቁ 9 ሎት 9. የአርክዌር ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ግንባታዎችንም ማሰራት ይፈልጋል ::
ስስሆነም በጨረታው ስመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በስራ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በተወዳደሩበት የሎቱ ብዛት በፖስታ በማሸግ ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ውድድር በጠቅላላ ድምር ሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲሞሉ የአንዱን ዋጋ ዝርዝር አይነት 15% ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰሜን ወሎ ዞን በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስተዳደር ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከነማስረጃዎቹ በታሸገ ፖስታ በድርጅት ስምና አድራሻ በመግለጽ በድርጅትዎ ማህተም ተረጋግጦ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 (ሰላሳ ) ቀናት አየር ላይ ውሎ (ክፍት ሆኖ ቆይቶ) በ31 ( በሰላሳ አንደኛው) ቀን 3፡30 ሰዓት ሲሆን ታሽጎ 4፡00 ሰአት ሲሆን በግዥ ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ተሸጋግሮ 3፡30 ሰዓት ሲሆን ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ ማሳወቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲያስይዙ ቫትን ጨምሮ የሞሉትን የጠቅላላ ድምር ሎት ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ኦርጅናሉን/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጨረታው ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ከታወቀ በኋላ አሸናፊው ውል ከወሰደ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይለቀቃል፣ የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠው የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ባልተረጋገጠ የባንክ ዋስትና (ኦርጅናሉን) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከውሉ ጠቅላላ ድምር ዋጋ ላይ በማስያዝ በጉ/ወ/አቃቢ ህግ ጽ/ቤት በኩል ውል ይወሰዳል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስቀጣል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-331-22-65 ወይም ዐ33-331-01-57 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የጉባ ላፍቶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ
ትብብር ጽ/ቤት
ወልዲያ