| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 13፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
Agricultural Transformation Agency
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
- ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት፡- ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ
- የጨረታ ቁጥር፡- ATA-NCB-W-2020-0018
- የጨረታው ርዕስ/ስያሜ፡- የገበያ መሽጫ ግንባታ
- ግንባታው የሚካሄድበት አካባቢ፡- በወረታ ከተማ ፎገራ ወረዳ አማራ ክልል
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አነስተኛ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዚሁ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ሆኖ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን
- ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግንባታ ሥራ ብቃት የሚያረጋግጥ ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በግንባታ ዘርፍ ስራ ላይ ቢያንስ ሶስት የግንባታ ስራዎችን ላለፉት አምስት ዓመታቶች በአመርቂ ሁኔታ ሰርቶ ያስረከበ ለዚህም ማረጋገጫ ሰርተፍኬት መያያዝ ይኖርባቸዋል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም በግዢ ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጫራቹ የቴክኒክ ብቃት፣ ክህሎትና ልምድ እንዲሁም ጥሩ የፋይናንስ አቅም እና አፈጻጸም መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃዎች ተሟልቶ ሊቀርብ ይገባል፣
6. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ዋና እና ኮፒውን የፋይናንስና የቴክኒክ ሰነዶችን በተለያዩ በሰም በታሸገ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተወዳዳሪዎች ለስራው የሚያቀርቡትን ዋጋ መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጃው የዋጋ ማቅረቢያ Bill of Quantity/ ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞልተውና ፈርመው እንዲሁም ማህተም አድርገው ሊያቀርቡ ይገባል ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 (ብር አንድ መቶ ሃምሳ ሺ/ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ ከሆነ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ118 ቀን የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።የኢንሹራንስ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
9. ጨረታው ታኅሣሥ 20 ቀን 2013 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ 8፡30 ሰዓት ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ባህርዳር ቅርንጫፍ ቢሮ የአረጋዊያን ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቀበሌ 14 በኦፕሬሽን ዳይሬክተር በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል::
10. በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 200.00 በመክፈል አዲስ አበባ ወይም ባህር ዳር ከሚገኘው ቢሮ ለማግኘት ይችላሉ።
11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ መጠየቅ ቢፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ።
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ አድራሻ
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ
ስልክ ቁጥር +251-115 -570678/85 /+ 251911-646029/ +251980527657
ኢሜል፡-yohannes.tadesse@ata.gov.et or abraham.shagrie@ata.gov.et
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፡- ከሱር ኮንስትራክሽን አጠገብ በሚያስገባው አስፓልት 1 ኪ.ሜ ያህል ገባ ብሎ ስተርሊንግ ህንጻ 7 ፎቅ ባህርዳር፡- የአረጋዊያን ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቀበሌ 14 ኦፕሬሽን ዳይሬክተር
ፋክስ + 251-115 570668
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ