| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 27፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check It!
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ፌ/ፖ/ኮ:-01/2013
የኢፌዴሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለ2013 በጀት ዓመት በድጋሚ የወጣ የዋናው ግቢ ዙሪያ አጥር ግንባታ (Control Room, Watch Tower, Fence $Electronic System Works) ለማሰራት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድሪጅቶች ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ (BC/GC Grade 4 and above) ያላቸው ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ ወቅታዊ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፊኬት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ፌ/ፖ/ኮ/ 01/2013 የዋና ግቢ ዙሪያ አጥር ግንባታ ለማሰራት 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (BID BOND) /CPO/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፌ/ፖ/ኮ/ 01/2013 የዋና ግቢ ዙሪያ አጥር ግንባታ ለማሰራት እስከ 29/3/2013 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዲቪዥን ቢሮ ቁጥር 203 ቀርበው የጨረታ ሠነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማሸግና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ወይም በመልዕከት ሣጥን ቁጥር 99 መላክ ይችላሉ፡፡ መ/ ቤታችን ስለጨረታ ሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከላይ በተገለፀው የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው በተመሳሳይ ቀን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት ትንሹ አዳራሽ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5-58 37-39/011-5-52-44-12/011-5-31-20-95/011-5-31-21-99 የውስጥ
ስልክ 2104/07/1101 ፋክስ ቁጥር 011-5-52-55-17 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን