Published on: Addis Zemen ( መስከረም 30፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-SSNI-T207
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በጐሬ መቱ ኤርፖርት የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ ዲዛይን እና ግንባታ (Design Build Project Delivery Method) ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮች (Design Build Contractors) በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በመንገድ ግንባታ (RC) ወይም ጠቅላላ ግንባታ (GC) ደረጃ 1 የሆነ እና የ2013 ዓም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ በጨረታ ሰነዱ መሰረት አስፈላጊውን መረጃ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨረታ ቁጥር (SSNT-T207) በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜል ያገኛሉ።
- ተጫራቾች በጨረታውደንብ መሠረት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል የመጫረቻ ሠነዳቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ግዥ ክፍል እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪኤሽን አካዳሚ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ርቀትን በጠበቀ ሁኔታ በተመሳሳይ ቀን ጥቅምት 24 ቀን 2013 በ9:30 ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ክፍል
በስልክ ቁጥር 0115174028 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
ኢሜል: Helenn@ethiopianairlines.com
Cc: YoditTk@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።