Published on: Addis Zemen ( መስከረም 24፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:አዳማ
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በከተማው የተለያዩ ስራዎችን ለማሰራት የተለያዩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት /ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
- ለተጠየቀው የማሽነሪ ኪራይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer registration No) ያላቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) ስጽ/ቤቱ ስም የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000000184369 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ሰነድ ላይ በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ብቻ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ ዋጋውን መሙላት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢ ሰነድ ላይ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ማቅረብ የሚጠበቅበት 1. ዌል እስካቫተር ባለ ጎማ(1) 2.ሩሎ (2) 3. ሎደር 3.5m2 (7) ሲሆን
- ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርባቸው ማሽነሪዎች ቦሎ ያስደረገበትን ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የነዳጅ ዋጋ እና የተለያዩ ጥገናዎችን በራሱ ወጪ የሚሸፍን መሆን አለበት።
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው ማሽነዎች አሮጌ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጪ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺ | ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር በአስተማማኝ ሁኔታ ስራውን ማከናወን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ መሆን አለበት፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-211-14-42 ላይ ማግኘት ይችላሉ።
የአዳማ ከተማ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት