| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 25፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ደብረ ዘይት |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የአስፋልት መንገድ ጥገና አገልግሎት ግዥ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር NVI 07/2013
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የውስጥ ለውስጥ የግቢ የአስፋልት መንገድ ጥገና አቅርቦቱና አገልግሎት ግዥበጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
- ተጫራቾች የ2013 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ደረጃቸው GC 5/ BC 4 እና ከዚያ በላይየሆኑና የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው መጀመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተያያዘው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም መሰረት በመሙላትየድርጅታቸውን ማሕተምና ፊርማ በማድረግ፣ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የዋጋቸውን 2% በሲፒኦቼክ በማስያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀናት ውስጥ የግዥ፤ ንብረትአስተዳደር እና የጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን 21ኛው ቀን በዓል ወይም እረፍትከሆነ በሚቀጥለው ቀን በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋም ሆነ በሌላ የጨረታ ጉዳይ ላይ ለውጥ ወይምማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተገለጹትን መስፈርቶች በሙሉ ማሟላት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ውል በመፈረም ሥራውን በአጭር ጊዜ መጀመር ይጠበቅበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ደብረ ዘይት ከተማ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ
ኮሌጅ አለፍ ብሎ ከእንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ አጠገብ
የበለጠ መረጃ ለማግኘት 011-433-83-39/011-4332117 መጠየቅ ይቻላል።
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት