Free
| Remaining time for BID submission |
| Invited Grade or Category | ከደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ |
| Place of competition | አዲስ አበባ |
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ
1. የጨረታ ቁጥር፡ ATA-NCB-W-2021-0001 ደቡብ
2. የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የደቡብ ሪጅን ቢሮ የኔት ሼድ የግንባታ ስራ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
| ሎት | ዝርዝር | ሳይት | ብዛት | የግንባታ ቦታ |
| 1 | ኔት ሼድ አቅርቦት እና ዝርጋታ ስራ | 1 | 1 | አርባ ምንጭ ጫኖ ሚሌ ቀበሌ |
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- i. ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር በዚሁ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ሆነው ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ii. የግንባታ ሥራ ብቃት የሚያረጋግጥ ከደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችሉ።
- iii. በግንባታ ዘርፍ ስራ ላይ ቢያንስ ሁለት የግንባታ ስራዎችን በአመርቂ ሁኔታ ሰርቶ ያስረከበ ለዚህም ማረጋገጫ መያያዝ ይኖርባቸዋል
- iv. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ
- V የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም በግዢ ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገቡ
- Vi, የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የሚያሳይ ማረጋገጫ የሚያቀርቡ
- vi. ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ
4. ተወዳዳሪዎች ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ የፋይናንስና የቴክኒክ ሰነዶችን ለይተው በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተወዳዳሪዎች ለስራው የሚያቀርቡትን ዋጋ መሥሪያ ቤቱ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተሞላ ዋጋ መቅረብ አለበት፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 / ሀያ አምስት ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው:የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ ከሆነ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀን የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንሹራንስ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው ከመወዳደራቸው በፊት ፕሮጀክቱ የሚገነባበት ቦታ (ሳይት አይተው መሙላት አለባቸው:: ይህን ሳያደርጉ ቀርተው ካሸነፉ በኃላ ከሳይት ልማት (and cleaning, land Cutting & filling or any Work related to site Work) ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ማንኛውም የቫሪየሽን ጥያቄዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
8. ጨረታው መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ የተጫራቶች የቴክኒክ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡
9. በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
10. ተጫራቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ ቢፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
አድራሻ
ስልክ +25115570665/0911715331
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ
Good Luck!