| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 3፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2013
የደብረ ፅባህ ቅዱስ ሚካኤል ሕንፃ አሠሪኮሚቴ እየተገነባ በሚገኘው ሕንፃ ቤተክርስቲያን ላይ ልዩ ልዩ
- የብረት ደረጃዎችን በራሱ ግብዓት ከነተጓዳኝ ዕቃዎች አቅርቦ ; ሠርቶና ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል ድርጅትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ማንኛውም በብረት ሥራ የተሠማራ ድርጅት ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣ ማግስት ጀምሮ በደብሩ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 50(ሃምሣ) በመከፈል ለመወዳደር ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ጋር በዘርፉ ያለውን የዕውቀትና የልምድ ዝርዝር መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታ ኮሚቴው የተጫራቹን የመሥሪያ ቦታ ለመጎብኘት እንዲችል ዎርክሾፑን በተፈለገ ጊዜ ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራች ድርጅቱ አስፈላጊ የሆኑትን የቴክኒክና የዋጋ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ አራት ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ቢሮ ማስረከብ ይገባዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ አራት ከሰላሣ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒክ ሰነዱ ብቻ ይከፈታል፡፡
- የዋጋው ኤንቨሎፕ የሚከፈተው በቴከኒክ ውድድሩ ያለፉት ተጫራቾች ሰነድ ብቻ ይሆናል፡፡ ጊዜውም በሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- ደብሩ ይህን ጨረታ በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብት አለው::
- ለማንኛውም ጥያቄ በስልክ ቁጥር 0911407807 መጠቀም ይቻላል፡፡
- አድራሻ፡- ከመገናኛ በጉርድ ሾላ ወደ ሲኤምሲ ሲኬድ የሰአሊተ ምኅረት ቤተክርስቲያንን አለፍ ብሎ በስተግራ አዲስ እየተሠራ ያለው የቅዱስሚካኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡
የደብረፅባሕ ቅዱስ ሚካኤል ሕንፃ
አሠሪ ኮሚቴ