| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 19፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማ |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር SRS-IBDB/JIW/19/2013
የሶማሌ ከልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ የዊብ ወንዝ በጨረቲ ወረዳ የመስኖ ዝርጋታ ስራን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ እና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጅግጅጋከሚገኘው የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በመገኘት የስራውን ዝርዝርና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መግዛት ይቻላሉ።
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ስራ ላይ የሰሩ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በስምንተኛውየስራ ቀን ከሰአት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከሰዓት 8፡30 መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት ጅግጅጋ ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር +251257753595/96
ፋክስ ቁጥር +251257753598 ጅግጅጋ ሶማሌ ክልል
የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ