| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 13፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በዋር ኮሌጅ ግቢ ውስጥ እያስገነባ ላለው ሕንፃ የሚያርፍበት የመሰረተ ቁፋሮ ሥራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ BC ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑትን የኮንስትራክሽን ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ድርጅቶች ተወዳድራችሁ መሥራት ስለምትችሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ በግብአት አቅርቦትና ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ ገዝታችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰባተኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡15 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን፤ ሰባተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በማግስቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡15 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡
- የግብር ከፋይ (TIN NO) ኮፒ ይያያዝ
- የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቆሬ አደባባይ
ለበለጠ መረጃ፡- ስቁ.- 011-8-72-11-74 ወይም 0118 72 03 83
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቆሬ አቅም ግንባታ ኮሌጅ ፕሮጀክት