The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የመማሪያ ክፍል ህንፃ ለማሰራት…

Published on:Be’kur ( ኅዳር 7፣ 2013 )Place of Bid Competitions:የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ያሉትን

  • ሎት 1፡-የመማሪያ ክፍል ህንፃ ብሎክ አንድ ፣
  • ሎት 2፡- የመማሪያ ክፍል ህንፃ ብሎክ ሁለት ፣
  • ሎት 3፡-የተማሪዎች ሻይ ቤት ህንፃ ፣የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ሻይ ቤት ህንፃና ንብረት ክፍል ህንፃ እና
  • ሎት 4፡-የአስተዳደር ቢሮ ህንፃና ሁለገብ አደራሽ ህንፃዎችን ጥገና እና እድሳት ለማሰራት GC & BC ደረጃ 7 እና በላይ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ህንፃዎችን ለማስጠገንና ለማሳደስ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ

በጨራታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠየቁትን ግዴታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1.  ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግዥ መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ እና እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ባዘጋጀው የጨረታ መመሪያና እስፔስፊኬሽን መሰረት መጠገንና ማደስ የሚችሉ፡፡
  4. 4ኛ.አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው በሞላው ጠቅላላ ዝቅተኛ የአንዱ ሎት/ጥቅል/ ዋጋ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የአንዱን ሎት ሁሉንም ጥገና እና እድሳት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨራታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  5. ተጫራቾች መወዳዳር የሚችሉት ከአንዱ ሎት-ጥገና እና እድሳት ላይ ብቻ ነው፡፡በመሆኑም ከአንድ ሎት- ጥገና እና እድሳት በላይ ተወዳድሮ የተገኘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 27/03/2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት የሚችል ሲሆን፤የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ ቅፅ ሞልተው ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር የጨረታ ሰነዱን እና የጨራታ ማስከበሪያውን ቢድ ቦንድ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተመሰከረለት ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የምታሲዙ ከሆነ በኮሌጁ ገቢ ደረሰኝ ገቢ አድርጋችሁ የደረሰኙን ኮፒ ከሰነዳችሁ ጋር አያይዛችሁ፤ አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ከቀን 07/03/2013 ዓ.ም እስከ 28/03/2013 ዓ.ም 3፡45 ድረስ እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግዥ፣ፋይናንስና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥ ላይ ተሳትፈው በውለታችሁ መሰረት ባለመፈፀማቸዉ ምክንያት ስልጣን ባለው አካል እገዳ ያልተደረገባችሁ መሆን አለበት፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 28/03/2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡45 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፤ተጫራቾች በመክፈቻዉ ዕለት ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ ይከፈታል፡፡ሆኖም ግን 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. . አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ግዥ ፈጸሚ አካላት አሸናፊው ተጫራች የሚጠግነውንና የሚያድሰውን መጠን ወይም ብዛት 20 በመቶ መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  11. . እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጨራቾች ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃፀም መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዢ ይሆናሉ፡፡ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ -0588279045 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page