| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 30፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check It!
የጨረታ ማስታወቂያ
የላፍቶ ቁጥር አንድ/1/ ኮንዶሚኒም የጋራ ቤቶች የሕ/ስራ ማህበር የግቢውን ዙሪያ የግንብ አጥር በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ።
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሆን አለባችሁ።
- BC/GC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያለው መሆን ይኖርበታል።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ /የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN Nuhber/ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ከፋይናንስ ቢሮ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ በማህበሩ ፅ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት በማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛል ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ጋር አብሮ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡-ላፍቶ ቁጥር አንድ/1/ ኮንደምኒየም
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-41-99688/0911824025
የላፍቶ ቁጥር አንድ/1/ ኮንዶሚኒም የጋራ ቤቶች የሕ/ስራ ማህበር