| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 19፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ካፋ ዞን |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
ካፋ ዞን የሺሾ-ኢንዴ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ 2013 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን ማለትም
- ጽሕፈት መሳሪያ፣
- የኤሌክትሪክሲቲና፣ ኤሌክትሮኒክስ፣
- የአይሲቲ፣
- ብረታብረት፣
- ጀኔራል ሜታል ፋብሪኬሽን፣
- የህንፃ ኮንስትራክሽን ፣
- ሳኒተሪ ኢንስታሌሽን፣ አውቶሞቲቭ ለሚሰለጥኑ ሰልጣኞች የሚያገለግሉ የሙያ መሳሪያዎችን፣
- የቢሮ ፈርኒቸር እና
- ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስስሆነም፤ ተወዳዳሪዎች፡-
- በሙያ መስክ ወይንም በዘርፉ የተመዘገቡና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው በፋይናንስ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የተጨማሪ እሴት ታከስ VAT ከፋይ ስለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘቡ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው::
- የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ Specification/ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ3ኛው ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ሳይጨምር ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት አዲስ አበባ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኘው ካፋ ፎረም ጽ/ቤት እና የሺሾ-ኢንዴ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትራል ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል::
- የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች በመለየት በአይነታቸው የሚሸጥበትን ነጠላ ዋጋ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ዋናና ኮፒ በማድረግ የሚጫረቱበትን ዘርፍ የተጫራቾችን ሥም /ድርጅት /በመፃፍ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 10ኛ ቀን ጀምሮ ቅዳሜ ጨምሮ ለ6 /ለስድስት ተከታታይ ስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ይሁንና የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ቀን አንስቶ አስረኛውን ቀን ሳይጠበቁ መመለስ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000 አምስት ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል:: ለዚህ ጨረታ ቢድ ቦንድ Bid bond/ ማስያዝ ተቀባይነት አይኖረውም::
- አሸናፊዎች ባሸነፉበት የዕቃ ዋጋ መጠን የውል ማስከበሪያ 10 % ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- በጨረታው የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃውን እስከ ሺሾ-ኢንዴ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትራል ኮሌጅ ድረስ የትራንስፖርትና ማንኛውንም ወጪ በመቻል በውሉ ላይ በሚጠቀሰው ቀን ማቅረብ አለባቸው:: ለማያቀርቡ ለውል ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም::
- ማንኛውም ተጫራች መጫረት የሚችለው በተሰማራበት ዘርፍ ብቻ መሆን አለበት::
- ማንኛውም ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም::
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት እለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል::
- የጨረታሳጥን ማስታወቂያው እሁድን ሳያካትትበጋዜጣ ከወጣበት 15ኛው ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይታሸጋል::
- የጨረታው ሳጥን የሚካፈተው ልክ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ ዕለቱ የእረፍት ወይንም በዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለው ሥራ ቀን ይተላለፋል::
- የጨረታው ሣጥን የሚከፈተው ሺሾ-ኢንዴ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግቢውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል:: ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሣጥን መክፈት አያስተጓጉልም::
- በጨረታ ሰነድ ላይ ማንኛውም ማስተካከያ ማድረግም ሆነ ከቀረበው ሰነድ ውጪ መሙላት አይፈቀድም::
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በሰልክ ቁጥር- 09124-07467/0476680440/0476680450 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
የሺሾ- ኢንዴ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ