| Published on:Reporter ( ኅዳር 20፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 019/2013
የሕብረት ባንክ ኢማ አዲስ ከቀየረው የባንኩን የስያሜና የአርማ ለውጥ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባና አካባቢው እንዲሁም በልዩ ልዩ ክልሎች የሚገኙ በአጠቃላይ 140 የሚሆኑ የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ አይነታቸው እና ብዛታቸው ከዚህ በታች የተመለከቱት የሚፈርሱ
- ካውንተሮችን ፣አልሙኒየም ፓርቲሽን እና ብረታ ብረቶችን ባሉበት ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በየቅርንጫፎቹ በመገኘት በጥንቃቄ አፍርሶና አጓጉዞ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን ዝርዝር ዕቃዎችን በሚመለከት ከዚህ በታች እንደተመለከተው ቀርቧል።
| ተ.ቁ | የዕቃዎች ዝርዝር | ብዛት | ምርመራ | |
| 1 | ካውንተር ቁመቱ 110 ሳ.ሜ የተተከለበት ጥልቀቱ 65ሳ.ሜ እና አጭር የእንጨት በር ቁመቱ 110 ሳ.ሜ | ሜትር | 1,410 | ዕቃዎቹ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጭ በተለያዩ ክልሎች የባንኩ ቅርንጫፎችየሚገኙ ናቸው |
| 2 | አልሙኒየም ፓርቲሽን | ካ.ሜ | 6,120 | |
| 3 | ብረታ ብረቶች | ካ.ሜ | 650 |
- ከላይ የተዘረዘሩትን ልዩልዩ ዕቃዎች ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ3፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 እስከ10፡00 ሰዓት ድረስ ዕቃዎቹ በሚገኙበትና በተገለፁት የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን መግዣ በነጠላ ወይም በጥቅል ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የሚቀርበው ዋጋ ተ.እ.ታን የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በመጫረቻ ሰነድ ላይ በተቀመጠው መሰረት በግልፅ ማስፈር አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሉ በመክፈል ዕቃዎቹን ተረክቦ አፍርሶ ማንሳት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ዕቃዎቹን የሚገዙበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና የቅርንጫፎቹን ስም ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ከክፍያ ነፃ በሆነ ሁኔታ የተዘጋጀ በመሆኑ፡-
- ሀ. አዲስ አበባ ከተማና በአካባቢው በቅርብ ርቀት የሚገኙ ተጫራቾች ወይም ገዢዎች በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሚክዎር ፕላዛ ሕንፃ ምድር ቤት የንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአየር ላይ እስከሚቆይበት ቀን ድረስ ከክፍያ ነፃ በሆነ ሁኔታ መውሰድ ይቻላሉ።
- ለ. በክልል የሚገኙ ተጫራቾች ወይም ገዢዎች በየክልሉ በሚገኙ የዲስትሪክት ቢሮዎች ወይም ዕቃዎቹ በሚገኙበት ቅርንጫፎች በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአየር ላይ እስከሚቆይበት ቀን ድረስ ከክፍያ ነፃ በሆነ ሁኔታ መውሰድ ይቻላሉ።
5. አዲስ አበባ ከተማና በአካባቢው የሚገኙ ተጫራቾች ወይም ገዢዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በባንኩ ዋና መ/ቤት ሚክዎር ፕላዛ ሕንፃ ምድር ቤት የንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
6. በክልል የሚገኙ ተጫራቾች ወይም ገዢዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በገዙበት ዲስትሪክት ቢሮዎች ወይም ዕቃዎቹ በሚገኙበት ቅርንጫፍች ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ ቦታ ማስገባት ወይም ማስረከብ ይችላሉ።
7. ጨረታው የሚዘጋው ሕዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው ደግሞ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት የቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
8. ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 0114-655222 /0114-169757 ሰውስጥ ቁጥር 250 ወይም 299 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
9. ባንኩ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ሕብረት ባንክ አ.ማ.