| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 26፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ የግብርና ኅ/ሥ/ማ/ፌዴሬሽን ሎት (የኩሉምሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት) እና ሎት 2 (የአጥር) በአሰላ ከተማ ለሚያስገነባው ግንባታ በኮንትራከተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
- የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ GC-5 /የህንፃ ስራ ተቋራጭ BC-4 ንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ጨረታ ሰነዱን በቂርቆስ ክ/ከተማ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ቦሌ መድሐኒአለም መንገድ 300 ሜትር አዲስ አበባ መስተዳድር ጤና ቢሮ ወይም የኦሮሚያ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ ኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ጽ/ቤት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቶች በዚህ የንግድ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ 90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ /ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እና በተጨማሪ ከጨረታ መክፈቻ ቀን በኋላ የ 28 ቀን ዋስትና የሚሰጥ መጠኑም 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) የሆነ እና ለብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ከቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት
- 5.1 ጨረታው (የቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ) በ22ኛው ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- 5.2 የቴክኒካል ሰነድ ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም የታሸገ ኢንቨሎፕ ተደርጎ እንዲሁምኦርጂናል እና ኮፒውን በአንድ ላይ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- 5.3 የፋይናንሺያል ሰነድ ኦርጂናል እና 1 ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም የታሸገ ኢንቨሎፕ ተደርጎ እንዲሁም ኦርጂናል እና ኮፒውን በአንድ ላይ በሰም የታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- 5.4 የቴክኒካል ሰነድ ጨረታው በገባበት በዚያው ቀን የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ማህበራትፌዴሬሽን ቢሮ ውስጥ ይከፈትና ለግምገማ ለጨረታ ኮሚቴ ይተላለፋል፡፡
- 5.5 የፋይናንሽያል ሰነዱ የጨረታ ኮሚቴው በተገኘበት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የፋይናንሺያል ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ታሽጎ ይቆያል፡፡
- 5.6 የጨረታው ኮሚቴ በተዘጋጀው የጨረታ መስፈርት መሰረት የቀረበውን የቴከኒካል ሰነድ መርምሮ በጨረታው ሰነድ መሰረት የተጫራቾችን ውጤት ያስቀምጣል፡፡
- 5.7 የፋይናንሺያል ሰነድ በፋይናንሺያል ሰነድ መከፈቻ ቀን የሚከፈትላቸው ተጫራቾች በቴክኒካል መስፈርት የማለፊያ ላስመዘገቡት ሲሆን የቴክኒካል ሰነድ ላላሟሉ ተጫራቾች የፋይናንሺያል ሰነዳቸው ሳይከፈት ይቆያል፡፡
- 5.8 የተሳሳተ መረጃ፣ የሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መስጠት እና የቴክኒካል ሰነድ ላይ ዋጋ ማሳወቅ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡
- 5.9 ፌዴሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ተጫራቹ ጥሩ የመልካም ስራ አፈፃፀም ሪከርድ ከሌለው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
6. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፌዴሬሽኑ መረዳት ይቻላል፡፡
- አድራሻ፡-የኦሮሚያ የግብርና ኅ/ሥ/ማ/ፈዳሪሽን
- ስልክ 011557 6182/84 ፋክስ 0115576180
- የኦሮሚያ የግብርና ኅ/ሥ/ማ/ፌዴሬሽን