| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 28፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዳማ ከተማ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check It!
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በስሬ ፣ ድክሲስ፣ አርቦዬ፣ጃራ፣ አዳባ እና በአጋርፋ ክዎስክ ሾፕ የሪኖቬሽን ስራ REQ No:4046336, 4046339, 4046342, 4046343, 4046344 እና 4046345 ቅደም ተከተል በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሶስት ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
መስፈርት:
- ጨረታው ከጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 15,000.00/አስራ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994/022-1 12-16 60 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን