| Published on:Reporter ( ኅዳር 13፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የመጸዳጃ ቤት ግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት CCRDA ከ400 በላይ አባላት ያሉትና ከ46 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው:: ድርጅቱ አንድ አነስተኛ መጸዳጃ ቤት በቅጥር ጊቢው ውስጥ ደረጃው 7 እና ከዚያ በላይ በሆነ የህንፃ ተቋራጭ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል:: በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ባለሞያዎች ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 103 የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል የግንባታውን መመሪያ ሰነድ ወስደው ከተመለከቱ በኋላ፤
- የግብር ከፋይ (Tin No) ቅጂ
- የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ቅጂ
- የታደሰ የሥራ ፈቃድ ቅጂ በማያያዝ
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሚሠሩበትን የእጅና የእቃ አጠቃላይ ዋጋ እንዲሁም ለሥራው ዋስትና የሚሆን ብር 3000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ስታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 304 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና የልማት ማህበራት ህብረት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
የከርስቲያን በጎ አድራጎትና የልማት ማህበራት ህብረት
አድራሻ፤ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት
ስልክ 0114-390322 ወይም 0114-393393