| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 6፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ኦሮሚያ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የገላን ከተማ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት ለከተማ የሚውል አስፓልት መንገድ ደረጃው (አንድ ) የሆነ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በ2013 የበጀት ዓመት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ደረጃው አርሲ/ጂሲ-( RC/GC-) እና ከዛ በላይ የስራ ተቋራጭ የሆነ፤
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድና ሥራ ፍቃድ ያለው፣
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- የቫት /የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin/ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ስለመልካም ስራ አፈጻጸም በግንባታ ዘርፍ የሰሩበት መረጃ ቢያንስ ሶስት መንግስታዊ ወይምመንግስታዊካልሆነ ድርጅቶች የተሰጠ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤ ሆኖ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከገላን ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ቀርቦ መግዛት ይችላል፡፡ነገር ግን የጨረታ ሰነዱን ከገላን ከተማ አስ/ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት መውሰድ ይቻላል፡፡
- የ2013 ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይምከኦሮሚያኮንስትራክሽን ቢሮ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ለውድድር ያስገባችሁትን ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከኦርጅናል ዶከመንት ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ በቁጥር እና በፊደል ያለምንም ስርዝ እና ድልዝ በመሙላት ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ሰነድ ላይ ማኖር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነት ከተገለጸላቸው በኋላ በተገለጸላቸው ቀን ቀርበው ውላቸውን ካልፈጸሙ የጨረታው ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ሥራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥን መከፈቻ ስነ ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
- የመንግስትን የፋይናንስ መመሪያን የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግዎ በሰልክ ቁጥር 0114450182 ደውለው ይጠይቁ፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት
የገላን ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት