| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 7፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን ማሻ ከተማ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002
ሀ/ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለማሻ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ት የሚውል
- ሎት 1 ባለ 1ሜር ቱቦ ማምረት
- ሎት 2 ቱቦ ቀበራ
- ሎት 3 ዲች ቦይ ግንባታ በየሳይቱ
- ሎት 4 ጠጠር 002 እና 003 ግዥ
- ሎት 5 ቅዳሜ ገበያ ሜዳ የከብት በረት አጥር ማሳጠር
- ሎት 6 ጋራጋንቲና ጠጠር በራሱ ሎደር እና ገልባጭ መኪና ባለ10 ጎማ 14 ሜትር ኪዩቢ ጭኖ ከ 5 -7 ኪሜ ራድየስ ውስጥ ለውስጥ ማራገፍ የሚችሉ የግል ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማጫረት ይፈልጋል
ለ/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ ላይ መሳተፍ ይችላሉ
- በመስኩ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በ2013 በጀት ዓመት የታደሰ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ገልባጭ መኪናዎችና ሎደር ማከራየት የሚችሉ የባለንብረትነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉና የራሱ ካልሆነ የአከራይ ተከራይ ውል ማቅረብ የሚችል የገልባጭ ብዛት ቢያንስ ሁለት ሲሆን ሎደር አንድና ከዚያ በላይ ሆኖ የገልባጭና ሎደር ሊብሬና ሦስተኛ ወገን ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- የመኪናውን ስፋትና ጥበትን በመጀመሪያ ማስለካት የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ከላይ ሎት 4 እና 6 ላይ ለተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ የሚችል
- ከላይ 1.2.3 እና 5 ለተጠቀሱት ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000 ብር /አራት ሺህ ብር/በባንክ የተረጋገጠ CPO/ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ
- ከላይ በሎት 1- 6ኛው ላይ ለተጠቀሰው ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት ገንዘቡን በመከፈል ደረሰኝ በመያዝ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ-8 ቀርበው የጨረታ ሠነዱን መውሰድ የሚችል
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ በመሙላት ሠነዱን በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በመለየት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ፊርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በ22ኛው ቀን በማሻ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል
- 22ኛው ቀን የመንግስት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ መ/ቤቱ የሚፈልገውን ገልባጭና ሎደር በሎት 6 ላይ ያለውን ጨረታ ያሸነፈ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ በዞኑ ዋና ከተማ ማሻከ/ፋ/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት
- የጨረታ አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በተገለፀ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው። በጨረታ ሠነዱ በቀረቡት መስፈርቶች መሠረት በወቅቱ በጥራት በተፈለገ ቦታ እስከ ሳይት ድረስ ማቅረብ ግዴታ አለበት ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 0475580530 /0474522817 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ በሸካ ዞን
ማሻ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት