| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 18፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
በፋና ቦሌ ሸማቾች/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር የ17/19 ሕብረተሰብ ልማት ማዕከል የመናፈሻ ብፌ ቤት ግንባታና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎችን ማዕከሉ በሚሰጠው ዲዛይንና ስፔስፊኬሽን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል::
በዚሁ መሰረት ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ያሉ ኮንትራክተሮች /ባለሙያዎች/ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ትችላላችሁ::
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም የሥራ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
- ሰነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንድ በላይ መውሰድ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የስራቸውን የዋጋ ዝርዝርና ጨረታ ማወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ አካቶ ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም ኮንትራክተሮች የጠቅላላ ዋጋ የጨረታውን 2% በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታውን ቅዳሜ በ29/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡10 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ይዘጋና በእለቱ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር 17/19 ህብረተሰብልማት ማዕከል አዳራሽ ይከፈታል:: የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡ ይህ ከሆነ ተጫራቹ ያስገባው ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 የስራ ቀናት የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር 17/19 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል በመቅረብ ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ከታሸገና ሰነዶቹ መከፈት ከተጀመረ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም: የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
- የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር 17/19 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአትላስ ወደ ደሳለኝ ሆቴል በሚወስደው
አስፓልት በግምት 200 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ከሩዋንዳ ወደ
ደሳለኝ ሆቴል በሚወስደው አስፓልት በግምት 100 ሜትር ላይ ያገኙታል፡፡
ለበለጠ መረጃ 011 618 36 70/ 011 662 44 42
የፋና ቦሴ ሸማቾች/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር