The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

በየወረዳው ት/ቤቶች የሚሰሩ የመመገቢያና ማብሰያ ክፍሎች…

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 11፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

በድጋሚ የወጣ አስቸኳይ የጨረታ

ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት ስር ከሚገነቡ ግንባታዎች ውስጥ በየወረዳው ት/ቤቶች የሚሰሩ የመመገቢያና ማብሰያ ክፍሎች ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ኃይልና ማሽነሪዎችን በማሟላት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎቶች የሚሠሩ ደረጃ 5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ በሕንፃ ወይም ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን (BC/GC-5) በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

የሎት ቁጥር የፕሮጀክቱ ዓይነት የሚገነባበት ት/ቤትየሚሠራበት ወረዳ
ሎት 1መመገቢያ እና

ማብሰያ ክፍሎች


ተስፋ KG04
ጎፋ KG
05
ነጻነት ጮራ KG05
ሎት 2መመገቢያ እና

ማብሰያ ክፍሎች


ሙሴ KG08
ኢጋዚያን KG08

ከላይ በተጠቀሰው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ለሥራው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 የሥራ ቀናት ብቻ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በመከፈል የጨረታውን ሠነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሽያል 2 ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል ለየብቻው እንዲሁም ቴክኒካል 2 ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል ለየብቻው በማሸግና CPO ኦርጅናል ቴክኒካል ሠነድ ውስጥ ብቻ አሽጎ በማስገባት፣ እንዲሁም ለየብቻ የታሸጉትን የቴክኒካል ሠነዶች ሦስቱን አንድ ላይ በማሸግ፣ ለየብቻ ሦስቱን የታሸጉትን የፋይናንሺያል ሠነዶች አንድ ላይ በማሸግ በመጨረሻም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ መመሪያው በሚያዘው መሠረት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ እስከ 4፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱልክ በ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) በክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀን የሚቆይ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡

  • ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ከቴክኒካል ኦርጅናል ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሠነድ ላይ ትክከለኛ አድራሻቸውን የፕሮጀከት ባለቤቱን አድራሻ በመፃፍ እንዲሁምመፈረምና ሕጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  • በክ/ከተማው ሥራ ያላቸው ተቋራጮች ሥራውን ከ70% በላይ ስለማድረሳቸው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አያይዘው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ስርዝ ድልዝ መረጃና ዋጋ ማቅረብ ከጨረታው ያሠርዛል፡፡ .ተጫራቹ ከአንድ ሎት በላይ ከተጫረቱ ከጨረታው ያሠርዛል፡፡ኣሠሪ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  • አድራሻ፡- ለቡ መብራት አደባባይ አጠገብ ሴፍዋይ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03
  • የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page