| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 13፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ብ/ግ/ጨ/ESSTl/NCB/03/2013
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በእንጦጦ ኦቭዞርቫቶሪና ምርምር ማዕከል ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች አማካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዘጋቢ እና ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዥ ሲመጡ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
| ሎት ቁጥር | የሚፈፀመው ግዥ | የጨረታ ማስከበሪያ | መግለጫ |
| 1 | በእንጦጦ ኦቭዞርቫቶሪና ምርምር ማዕከል የግንባታ ስራዎች የምክር አገልግሎት | ብር 20,000 | ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ |
4. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢንስቲትዩቱ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
5. የጨረታ መክፈቻ ቀን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው መጀመሪያ የስራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጠለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡አዲስ አበባ ጉለሌ ወረዳ 2፣ የቤት ቁጥር 179
የስልክ ቁጥር ፡ 011872- 0257
ምስካየ ህዙናን ቤተክርስትቲያን ፊት ለፊት ወደ መነን
በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ህንፃ
በኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት