Published on:Addis Zemen ( መስከረም 17፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:የየም ልዩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት
Remaining Time for Bid Submission
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መለያ ቁጥር 001/2013
የየም ልዩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጥ ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ::
| ተ.ቁ | የፕሮጀክቱ ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ /Cpo/ | ደረጃ |
| 1 | ሰሞናማ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች | 5,000 | 9ኛ ከዚያ በላይ |
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፈቃድና የዘመኑን የሥራ ግብር አጠናቀው የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የንግድ መለያ ቁጥር/Tin number/ ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር ለ21 ስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ፋይናሽያልና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በመጨረሻው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የም ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት በፋ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል ::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ሁኔታ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ከተረጋገጠ በኋላ ወዲያውኑ ሌሎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ይመለሳል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዝርዝር ዋጋ ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ለይቶ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብና ዋጋ ላይ ስምና ፊርማቸውን፣ ቀንና የድርጅቱ ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ሙሉ በሙሉ በውሉ መሠረት ማጠናቀቃቸው ከተረጋገጠ በኋላ ሙሉ ክፍያ ይከፈላቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው በበዓላትና በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ላይ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉለውም::
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ::
- ተጫራቾች የሥራ ፈቃዳቸው ያልተሟላ መረጃና የዋጋ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፡፡
- ለተደራጁ አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት ተሻሽሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 172/2011 በደንቡ መሠረት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
- የየም ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ሣጃ ከተማ ሲሆን ከአ/አ 240 ኪሜ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን፡፡
- አሸናፊው የሆነ ተጫራች ተቋሙ ቅድሜ ክፍያ ለመክፈል አይገደድም።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0474518006 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የየም ልዩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት