| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 22፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ሰበታ ከተማ |
Remaining Time for Bid Submission (Check it)
የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ሰነድ የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰበታ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለከተማው አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት መሰረተ ልማት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ
- ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል::
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታክስ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመክ ፈላቸው በቂ ማስረጃ (ከሊራንስ) አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሰበታ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ባንክ ሂሳብ ቁጥር በሆነው በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000010960596 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ከሰበታ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን 01 ቀበሌ በመሄድ ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ከሰበታ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ /ቤት ዘውትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO በሰበታ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ሰነዱ ላይ ፈርሞ በማህተም በማረጋገጥ በሰም ኤንቨሎን በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚትችሉ በመሆኑን፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፣ እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (56) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ማሽነሪ ሰበታ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀረቡት ማሽነሪ ቢያንስ በቀን ከ8፡00 ሰዓት በላይ የመሥራት አቅም ያለው እና አዲስ ሞዴል ማለትም ከ2012 ወዲህ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ማሽነሪ ዓይነት እና ሞዴል የሚገልጽ የባለቤትነት ሊብሬ ወይም የሕጋዊ ኪራይ ውል ከሊብሬ ጋር ከሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ማሽነሪ ኪራይ እስከ በጀቱ ዓመት መጨረሻ ደረስ ለማከራየት የሆነ መሆን አለበት።
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ሰነድ የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከላይ የተገለጸው የመከፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-
0113384292/0113382859
የሰበታ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ት/ጽ/ቤት