| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 10፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
በፋና ቦሌ ሸማቾች/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር የ17/19 ሕብረተሰብ ልማት ማዕከል የመናፈሻ ብፌ ቤት ግንባታና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎችን ማዕከሉ በሚሰጠው ዲዛይንና ስፔስፊኬሽን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል:: በዚሁ መሰረት ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ
ያሉ ኮንትራክተሮች /ባለሙያዎች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ትችላላችሁ::
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም የሥራ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
- ሰነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንድ በላይ መውሰድ አይችሉም::
- ተጫራቾች የስራቸውን የዋጋ ዝርዝርና ጨረታ ማወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ አካቶ ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም ኮንትራክተሮች የጠቅላላ ዋጋ የጨረታውን 2% በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 የስራ ቀናት የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር 17/19 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል በመቅረብ ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- 10ኛው ቀን በዋለ የመጀመሪያው ቅዳሜ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ይዘጋና በእለቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ ማህበር 17/19 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል አዳራሽ ይከፈታል:: የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም:: ይህ ከሆነ ተጫራቹ ያስገባው ሰነድ ውድቅ ይሆናል::
- የጨረታው ሳጥን ከታሽገና ሰነዶቹ መከፈት ከተጀመረ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል::
- የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር 17/19 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡ከአትላስ ወደ ደሳለኝ ሆቴል በሚወስደው አስፓልት በግምት 200 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ከሩዋንዳ ወደ ደሳለኝ ሆቴል በሚወስደው አስፓልት በግምት 100 ሜትር ላይ ያገኙታል፡፡
ለበለጠ መረጃ 011 618 36 70 / 011 662 44 42
በፋና ቦሌ ሸማቶች/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር
የ17/19 ሕብረተሰብ ልማት ማዕከል