| Remaining time for BID submission |
| Invited Grade or Category | CAE-1,CAE-3 እና በላይ, CAE-2 እና በላይ for d/t project |
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 004Sc /2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የዲዛይን ክለሳ፤ የክትትልና የቁጥጥር እና የውለታ አስተዳደር ስራዎችን የሚሰሩ አማካሪዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት
- ተጫራቾች ለሥራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝርየተመዘገቡ፤ወቅታዊ ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡና በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርኮንስትራክሽን ቢሮ አጭር ምዝገባ ያደረጉና የ2013 ዓ.ም ያሳደሱ የአማካሪ ድርጅቶች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ሎት 1 ጥሩነሽ ቤጂንግ ማስፋፊያ B+G+6 ህንፃ (CAE-1)
- ሎት 2 ሚኒሊክ ሆስፒታል ሬሳ ማቆያ (CAE-3 እና በላይ)
- ሎት 3 ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል B+G+8 ህንፃ (CAE-3)
- ሎት 4 ልደታ ወረዳ 02 አስተዳደር B+G+7 ህንፃ (CAE-2 እና በላይ)
- ሎት 5 ቂርቆስ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ (CAE-3 እና በላይ)
- ሎት 6 ቦሌ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት (CAE-5 እና በላይ)
- ሎት 7 አቃቂ ቃሊቲ አረጋዊያን ማቆያ ህንፃ (CAE-1)
- ሎት 8 የሴቶችና ህፃናት (CAE-3 እና በላይ)
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የስራ ቀናት ድረስ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በሰም በማሸግ የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራከሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት 11ኛው የስራ ቀን ድረስ ባለዉ ጊዜ እስከ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን (Technical & Financial Proposal ) ለእያንዳንዱ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የቅድመ ብቃት ጨረታ ሰነድ (Technical Proposal ) በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራከሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 801 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት በባንክ ከፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በፊት በቢሮአችን ስራ ያለው ከሆነ ከአንድ ሎት በላይ ምንም ስራ ከሌለው ደግሞ ከሁለት ሎት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-የጨረታ መክፈቻው 11 ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ
Good Luck!