| Published on:Be’kur ( ታኅሣሥ 19፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር የዳባት ወረዳ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር የዳባት ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በአልማ በጀት በጭላ ቀበሌ አንድ ብሎክ ባለ አራት ክፍል ትምህርት ቤት በሙሉ ዋጋ ለማስገንባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈለጋል:: ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላችሁ ተጫራቾች በውድድሩ እንድትሳተፉ እያሳሰብን ተጫራቾች ፡-
- ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የዘመኑን ግብር አጠቃሎ በመክፈል ንግድ ፍቃዱን ያደሰ፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ ቁጥር /ቲን/ ያለው/ያላት፣
- የግንባታ ፈቃዱ ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ፣
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1-4 የተመለከቱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የግንባታውን ሙሉ ስፔስፊኬሽን ወይም ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፣
- መ/ቤቱ 20 በመቶ ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 የኢትዮጵያ በእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ዳባት ወረዳ ግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ዋጋ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማለትም ግዥና ፋይናንስ ካርኒ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ በጨረታ ፖስታ ላይ በማሸግ ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሆኖ ለየብቻቸው ተለይተው ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ከታህሳስ 19/2013 ዓ.ም እስከ ጥር 3/2013 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 23 በቀን 4/5/2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ በ4፡30 ይከፈታል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ተጨማሪ ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ ዳባት ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 23 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 113 0410 ወይም 058 113 0205 በመደወል ማግኘት እንደሚቻል እናሳውቃለን::
ማሳሰቢያ ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል::
የዳ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት