| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 14፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አብክመ በደቡብ ወሎ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አብክመ በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የአር/ብ/ል/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የአር/ብ/ል/ወ/መንትራ ጽ/ቤት የ2013 የሥራ ዘመን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከአፈሶ አሞየ ሰርጤ ያሉትን መንገዶች ለማሰራት /አዲስ ቆረጣ ሥራ/፤ ጎበራ – ሀሮ – ጎቤሳ /ሰተዋ/ የማስፋፋት ሥራ ኤክስካቫተር የፈረስ ጉልበት 330 እና ከዚያ በላይ MODEL ከ2013 እና በላይ እንዲሁም ዶዘር የፈረስ ጉልበት 305 እና ከዚያ በላይ ሞዴል 2013 እና ከዚያ በላይ የሆነ ማሽን ተከራይቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መሥፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችል
- ቫት ቲን/ ተመዝጋቢ መሆኑን የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ድርጅት የጨረታ ሠነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 14/4/2013 እስከ 28/4/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአር ብ/ል/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 የማይመለስ ብር 100 ብር መግዛት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ድርጅት በገዛው የጨረታ ሠነድ ላይ ክብ ማህተምና ፊርማ በማድረግ የታሸገ ፓስታ እስከ 28/4/2013 ዓ.ም ድረስ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ሠነድ የሚታሸግበት ቀን 28/4/2013 ዓ.ም 10.00 ሰዓት ላይ ነው፡፡
- የጨረታ ሠነድ የሚከፈትበት ቀን 29/4/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ነው።
- ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 % የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ድርጅት ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታ ሠነድ በሚከፈትበት ቀን መኖር ይጠበቅበታል። ነገር ግን በራሱ ፍቃድ ባይገኝ በተላለፈው ውሣኔ ተገዥ ይሆናል።
- በጨረታ ሠነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ/ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆነ ነገሮች መኖር የለባቸውም።
- በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ውል ሲወስድ በአሸነፈበት ነጠላ ዋጋ ድምር የሁሉንም ሴክተር መ/ቤቶች መኪና ዋጋ ድምር የሚወስድ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ለናሙና የሚጠየቀውን ዕቃዎች ውል ከመፈፀሙ በፊት ማሳየት ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ድርጅት የአንድ ዋጋ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም።
- ጨረታው በሎት የተከፋፈለ ወይም በሎት የሚመደብ መሆኑ ይታወቃል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ፡-0921040410/0922939570
በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ መስተዳደር
ዞን አርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት